በእናት ታምናለህ?

< Do you believe in Mother

በእናታቸው ማህፀን ያሉ ሁለት ህፃናት ጨዋታ ይዘዋል፡፡አንደኛው አማኒ(ምዕመን) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ኢ-አማኒ ነው፡፡

ከውልደት በኃላ ህይወት እንዳለ ታምናለህ?

በእርግጠኝነት አዎ! ከውልደት በኃላ ህይወት እንዳለ ግልጽ ነው፡፡እኛ በዚህ የተገኘነው በቂ ጥንካሬ እንዲኖረን እና ወደፊት ለሚጠብቀን ኑሮ ዝግጁ እንድንሆን ነው፡፡

ምን አይነት ወለፈንዲ ነው የምታወራው? ከውልደት በኃላ ህይወትሊኖር አይችልም፡፡ህይወት ምን እንደሚመስል አሰበኸዋል?

ሁሉንም ነገር በጥልቀት አላውቅም ነገር ግን ከዚህ የተሻለ ብርሃን እንደሚኖርና ምናልባትም ልንራመድ እና በራሳችን አፍ ልንበላእንደምንችል አምናለው፡፡

ምኑ የማይረባ ነው! መራመድ እና በአፍ መብላት ፈጽሞ አይቻልም፡፡በጣምያስቃል! .....እትብት አለን በእርሱም እንበላለን፡፡ታውቃለህ! እኔ ልነግርህየምፈልገው ከወልደት በኃላ ህይወት እንደሌለ ነው፤ ምክንያቱም ዕትብታችን ህይወታችን ነው፤ እርሱ ደግሞ በጣም አጭር ነው ፡፡

እኔግን እንደሚቻል እርግጠኛ ነኝ፡፡ሁሉም ነገር በተወሰነ መልኩ የተለየሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን በደፈናው መገመት እንችላለን፡፡

እውነታው ግን ይሄ ነው፤ ከዚያ ማንም ሰው ተመልሶ አያውቅም፡፡በቀላሉ ህይወት በውልደት ፍጻሜውን ያገኛል፡፡በአጠቃላይህይወት በጨለማ ያለ፣ መጨበጫ የሌለው፣ ምቾት የማይሰጥ ነገር ነው፡፡

አይደለም!በጭራሽ እንዲህ አይለደም፡፡ከውልደት በኃላያለው ህይወታችን እንደሚመስል ጠንቅቄ ባለውቅም በማንኛውም መልኩ ግን እማዬን እናያታለን ፤ እርሷም እኛን ትንከባከበናለች፡፡

እማዬ!!!!! በእናት ካመንክ እሺ እርሷ የታለች?

እርሷ በእኛ ዙርያ የመላች ናት፡፡እኛ ህልው የሆነው በእርሷ ውስጥ ነው፤ በእርሷ ህያዋን ሆነን እንኖራለን እንንቀሳቀስማለን፡፡በቀላሉእኛ ያለ እርሷ የለንም፡፡

በአጠቃላይ ወለፈንድ ነው! ምንም እናት አላየሁም፤ስለዚህ እዳው ገብስ ነው እርሷም ህልው አይደለችም፡፡

ካንተ ጋር በዚህ አልስማማም፡፡እርግጥ አንዳንድ ጊዜ በዙሪያችን ያለው ነገር ሲረጋጋ እና ጸጥ ሲል እናታችን እያዜመች የእኛንአለም እንደምትዳብስ መስማት ይቻላል፡፡እኔ ትክክለኛው ህይወታችን የሚጀምረው ከተወለድን በኃላ ብቻ መሆኑን አምናለው፡፡ አንተስ?

ለኔ እዚህ እስካለው ድረሰ አይጨንቀኝም፡፡ እኔ ምፈልገው በዚህቦታ በምቾት መኖር እና ወደፊት የፈለገው ነገር እንዲሆን መፍቀድ ነው፡፡ እየኖርን የሚሆነውንእናያለን፡፡ዝማሬ እና ዳበሳ ላልከው እርሱ የማህጸን ውሳጣዊ ዓለም ህግነው፡፡

ነገር ግን ዓለም በራሱ እንዲህ ውብ አድርጎ አይዘምርም፡፡የዝማሬውንግጥሞች አድምጥ፡፡እናታችን እንዴት በፍቅር እንደምትጠራንም አስተውል፡፡

እና ፍቅር ምንድን ነው? እዚህካንተ ጋር እየኖርን ነው፤ ተግባብተናል ፡፡ይሄ ደግሞ ሰናይ ነው፡፡

በዝግታ እየተወዛወዙ ጨለማ ውስጥ መኖር ይቻላል ነገር ግን እኔ እየነገርኩህ ያለሁት ስለ ብርሃን ነው፡፡ ለመጀመሪያጊዜ እያለቀስን ብርሃንን ስለምናይበት ጊዜ፤ ወደ እናታችን እንመጣለን፤ በፊቷም ማልቀስ እንጀመራለን ምክንያቱም ለህማም አጋልጠናታል፡፡በአኮቴትምአዲሱን አለም መቀላቀል ይገባናል፡፡

እናታችን ምን እንዳዘጋጀችልን ማየት አትችልም? ለቅሶ እና ዋይታ!!!!!!! ለዚህ ደግሞ ማመስገን ይገባኛል?

ነገር ግን ከዚህ ደማቅ ብርሃን ባሻገር ችግሮችን ተቋቁመን እንድንኖር ጥንካሬን ያላብሰናል፡፡

እና ይህንን ደማቅ ብርሃን ለምን እፈልገዋለው ችግርን ተቋቁሞ መኖርንስ?

ስለዚህ ለዘለዓለም እንኖራልን፤ አንሞትምም፡፡እናታችንወልዳ ለሞት አሳልፋ አትሰጠንም፡፡ትሰጠናለች?

ምንጭ፥

Two babies chat in the womb of a pregnant woman. One of them is a believer and another one is a non-believer:
- Do you believe in life after birth?
- Yes, certainly. It is clear that there's life after birth. We are here to become strong enough and ready for what lies ahead for us.
- What nonsense! There can’t be life after birth! Can you imagine what that life would be like?
- I don't know all of the details but I trust that there will be more light and that we might even walk and maybe we will eat with our own mouths.
- What rubbish! It is impossible to walk and to eat with a mouth, it is comical! We have an umbilical cord which feeds us. You know, I want to tell you: it is impossible that there's life after birth because our life is an umbilical cord and it is already too short.
- I am sure that it's possible. Everything will be a little bit different but we can imagine it all.
- But it's a fact that nobody ever came back from there! Life simply comes to an end with birth. On the whole, life is a pointless misery in darkness.
- No, not at all! I don't know precisely how our life after birth will be but in any case, we will see Mum and she will take care of us.
- Mum? If you believe in a mother then where is she?
- She's all around us. We exist inside of her and we owe to it to her that we live and move about. Without her we simply can't exist.
- Total nonsense! I don't see any mum so it is obvious, that she simply doesn't exist.
- I can't agree with you. In fact sometimes, when all the things around us calm down, it is possible to hear her as she sings and to feel her as she caresses our world. I firmly believe that our genuine life will begin only after birth. What about you?
- As for me I don't mind it here. All I want is settle with some comfort in this place and then let be, what shall be. We shall live and we shall see. As to what you say about singing and caressing - that is the law of the intra-womb world.
- But the world in itself can't sing so beautifully. Listen to the Words of this song. Listen to how Mum calls us with her Love.
- And what is love? We live here with you and we get on, that’s good.
- It's possible to live creeping around in darkness but I speak to you about Light, about the time when we will see light and with our first cries, we shall come to Mum and start crying in front of her because we have caused her pain and then with gratitude we shall join the new world.
- Can’t you see what mum has prepared for us: screaming and crying and I should still thank her for it?
- But it will give us strength to survive despite such a bright light.
- And for what do I need such a bright light and to survive as well?
- So that we shall live eternally and not die. It can't be that Mum bore us for death, can it?